Pages

Wednesday, December 14, 2011

ያልተለቀሰለት ሙአች!

ሙሃመድ ቡአዚዚ (27)፡- ታህሳስ 17, 2010 ለቱኒዝያ ለውጥ እራሱን ሰዋ ህዝቡም በልቶ ማደሩን ሳይሆን ለተተኪው የሚያስተላልፈው ነገር ነበርና ሚያሰጨንቀው መልስ ለመስጠት ጊዜ አልወሰደበትም። በእርግጥ ቡአዚዚ በህይወቱ እራሱን ለማጥፋት የሚያነሳሳው ሱሱ ነው ወይስ ሃገር ስትገደል ስትታፈን ለማየት አልፈልግም ማለቱ ነው? ስለ ቡአዚዚ የተፃፉ ማጣቀሻዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን, ሃገር ወዳድ, ድህነትን ለማሸነፍ የሚሰራ, በትምህርቱ ካለበት የምጣኔ ሃብት ችግር የተነሳ ብዙም ያልገፋ ቢሆንም ግን ታናሾቹን እያስተማረ የነበረ ከሱሱ ጋር ምንም አይነት ግኑኙነት የሌለው። ግና መንግስት በህዝቡ ላየሚሰራውን አሻጥር ደባ በደል አይቶ ማለፍ ያልቻለ፣ ስራ አጥነት አድሎና ማግለል በሙስና የተዘፈቀ አሰራር ያማረረው  በመሆኑ ነበር። ይህን ያየ ህዝበ ቱኒዝያ የሰን ማገገም በጉጉት ሲጠባበቅ መንግስትም የተወሰነ የህክምና እርዳታ እያደረገለተ 18 ቀናትን መኖር ቻለ። በሆስፒታል በነበረበት ወቅትም የሚቃወማቸው ፕሬዝዳንት በመምጣት የተሻለ የህክምና እርዳታ ፈረንሳይ ሂዶ እንደ ሚያገኝ ቃል ገቡለት። ግና አልተደረገም ወይም አልተቻለም። ሄደ ላይመለስ, ግና እረፍተ ዜናውን የሰማ ህዝበ አረብ አለቀስ, የቻለም ቃል ገባ "ለሞትህ ምክንያት የሆኑትን እናባርራለን! " በሚል ዜማ። ቀብሩንም የጀግና አቀባበር ተቀበረ ከ5000 በላይ ለቀስተኛ ተሳታፊ ሆነ። ህዝቡም ቃሉን አከበረ ለጎረቤት ሃገር ህዝቦችም ትሚህርት ሰጡ። የዛ ህዝብ ተሞክሮ ለግብፅ፣ አልጄርያ፣ የመን፣ ሶርያ እንዲሁም የተለያዩ ይዘት ያላቸው የመብት ጥያቄዎች በአለም ተንሰራፉ የተወሰኑት ተሳኩ ሌሎች እስካሁን ተስፋ ባለመቁረጥ እየተካሄዱ ይገኛሉ።
ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባው የኛው ሰው እስቲ ህዝቤ ቢያለቅስልኝ በሚል እራሱን በእሳት አያያዘ። የኔሰው ገብሬ (35)። ህዝቡ  ሊያለቅስለት ሲገባ ያለቀሰበት ጀግና። በፖለቲካ አመለካከቱ ከስራ ተባረረ ሞቱም ከእብደት ጋር ተያያዘ ለማዳንም ምንም አይነት ሙከራ አልተደረገም በእርግጥ እብድ ከነበረ ለምን የተሻለ ቢያንስ ሪጅናል ሆሰፒታል አልተወሰደም? ለነገሩ ምን ያረጋል 1 ሰው ለዛውም የኔሰው ቢሞት ነው ሚሻለው ወንድም የለውማ ደሙን የሚፋረድ ፍትህን ሚያነፈንፍ ። ለመሃላው ሳይሆን ለደሞዙ የሚሰራ ዳኛ፣ አቃቢ ህግ እና ጠበቃ። ሃኪሙም ህዝቡን ከመርዳት ይልቅ መጉዳት የሚመኝ በስሙ ከሚነግዱት ጋር አብሮ የሚነግድ። መሃንዲሱም፣ ሙሁሩም ህዝቡም ለእድገት ማነቆ የሆነበትን አሰራር ከማውገዝና ከማስወገድ ይልቅ በአዩኝ አላዩኝ  ብቅ ጥልቅ የሚያጉረመርም። አኗኗርን  ከቀንድ አውጣ የተማረበት አመፁም የቀንድ አውጣ ኑሮውም የቀንድ አውጣ የሆነ ህዝብ ተፈጠረ። ይቀጥላል......