ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነፃነትን ፊልጋ ያልፈነቀለው
የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን አዋጅን ያውጅ ይሆናል እንጂ ጂሃድን አላወጀም ያውጃልም የሚል ስጋት የለኝም። አወጀ ሲሉ እንኳን በማን
ላይ በኬንያ፣በሱዳን፣በሶማሊያ ወይስ በኢትዮጵያ?። አቦ እናንተ እኮ እኔን ታናግሩኝ ጀመራቹ ። ይልቅ የህዝቡን ጥያቄ በቀጥታ መመለስ
የተሳነው የመለስ አሰተዳደር የህዝቡን ሰላማዊ ተቃውሞ ለግል ጥቅሙ እያዋለው ይገኛል። ይሀውም ባለፈው አርብ በአሩሲ የተገደሉ ንፁሃን
ሙስሊም ወንድሞቻችን አበይት ምሳሌ ናቸው። አቤ ቶክቻው እንዳስነበበን ከሆነ ሼህ ሱዑድ ሻሸመኔ በተካሄደዉ ስብሰባ ላይ “ኢህአዴግን ለሀያ አመታት ስንደግፈዉ ኖረን አሁን እንዴት አሸባሪ አክራሪ ብሎ ይወነጅለናል” ብለው ነበር። በመሆኑም እኝህ ሰው ትንሽ ከታገስኳቸው ለህዝቡ በስብሰባው የተደረገውን ጨምሮ በድሬ
ስለተካሄደው ሚስጥራዊ የአህባሽ አስተምሮ ጠመቃ ሹክ ሊሉ ይችላሉና ሰበብ ፊጥረን እናስወግዳቸው ይመስላል። “ሊያስሩት የፈለጉትን
ሼህ የአልቃኢዳ መሪ ነው! ” ይላሉ አለ አሽብር!
የባሌ ሙሰሊሞች ግን መቼ ነው እፎይ! የሚሉት ሲወርድ ሲዋረድ መንግስት ቢቀየርም
ለነዚህ ህዝቦች ያለውን አመለካከት የቀየረ ይመስላል እንጂ አይቀይርም። እነሱም ጥንካሬ ከሚነላህ ተሰጥቶአቸው አይንገዳገዱም። አቦ
አላህ ፈጣሪ ይጨምርላቸው። መሌ አሚን አትልም? ድሮ የዚህ አካባቢ ሰው ቃሊቻ ይሉት ነበር እነሆ ወሃቢያ አሉት ከዛም አልቃኢዳ
ጨመሩለት። ምን ነበር አልቃኢዳ? መንግስት ግን አሁን አገሪቱን መግዛት የከበደው ይመስላል። ለአገዛዝ እንዲመች ተከፋፈልን በክልል
ግን በቂ አይደለም በመሆኑም በሃይማኖት መከፋፈል አማራቹህ በሃይማኖት
መክፈል ግን ቀላል አይደለም እኮ ለነገሩ እርጉዝ የአውራ ዶሮ እንቁላል አማረኝ ብትል ምን ማድረግ ይቻላል?።
ህዝቡም አዋጅ አወጀ አዋጁም « መንግስት ሆይ! ሀገሬን ምራ እንጂ ቤቴን ለኔ ተውልኝ እኔም ለልጄ እማኖትን አሰተምረው ቢሆን እንጂ አልመርጥለትም!» ግና መንግስት ጅሃድ አደረገው። በፓርላማም ተናገረ። በአሩሲም ገድሎ አስነገረ 7 ግድሎ 10 እንደቆሰሉበት። ይሁና!
No comments:
Post a Comment