Pages

Friday, July 15, 2011

ፐሮጀክተር(projector)

አገልግሎት፡- የኮምፒዩተራችን፣ የዲቪዲ ወይም የዴክ በጥቅሉ ከማንኛውም ቪድዮ ምስል ከሚያሳዩ video port ካላቸው ኤሌክተሮኒክ መገልገያዎች (device) ጋር በማገናኘት የሚታየውን ምስል ሰፋ ባለ መስኮት (wide screen) ለማየት የሚያሰችል ነው። በአሁን ጊዜ በሃገራችን በስፋት በትምህርት ተቋማት ለማሰተማሪያነት፣ በዲሰቲቪ ክፍሎች ፣ በተለያዩ ድርጅቶች( የግልም የመንግስትም) አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል። ይህ እቃ በብዛት ምስሉን አቡጀዴ ወይም ነጭ ግድግዳ ላይ እንዲያንጸባርቅ ተደርጎ ሌሎች የነጸብራቅ ምንጮች ቢዘጉ (ማብራት ማጥፋት ወይም መጋረጃ መጋረድ) ምስሉን በደምብ ለማየትና ለተመልካች እንም የሚስብ ይሆናል።

አጠቃቀም፡- በመጀመርያ የፕሮጀክተሩን ገመድ(data cable VGA or DVI) ከመሳሪያው (device) የቪዲዮ ፖርት ላይ መሰካት ከዛም ከፕሮጀክተሩ ላይ መሰካት። በመቀጠል ሶኬት (power cable) መሰካትና ፐሮጀክተሩን ማብራት፥ለማብራት (on/off) ቁልፉን አንዴ መጠንቆል። ለማጥፋት ግን (on/off) ቁልፉን ተጭነን እስኪጠፋ መያዝ ይኖርብናል። ኮምፒዩተሮን ያብሩት ምስሉ በቀጥታ መታየት አለበት ካሆነ ግን እንደኮምፑተሮ ሞድል ከሚከተሉት ቁልፎች አንዱን ይሞክሩ ። shift + f4/f5/f6
ወይም በቀጥታ ዊነዶውስ እና ፒ (windows +P) በመጫን የፕሮጀክተር መቆጣጠሪያውን ይክፈቱ በቀላሉ የሚገባ በመሆኑ በጥሞና ያንብቡት።

ከዚህ በታች የ windows 7 አማራጮችን አቀርባለሁ።
  • Computer only (ይህ አማራጭ ምስሉን ከኮምፒዩተሮ ላይ ብቻ ለማየት ሲፈልጉ.)
  • Duplicate (በኮምፒዩተሮና በፕሮጀክረሩ ማየት ሲሹ.)
  • Extend (ከኮምፒየተሩ ለመቀጠል ይህ አማራጭ በብዛት ጥቅም ላይ አይውልም.)
  • Projector only (ፕሮጀክተሩ ላይ ብቻ.)
 በሚቀጥለው እትሜ አይነቱን በዝርዝር እና ተጓዳኝ እቃዎቹን ለማቅረብ ሞክራለሁ። ሠላም ለናንተ!
 የበለጠ ለማወቅ ይጠይቁ ወይም የሚከተሉትን ያንብቡ። ካነበቡ አስታየቶን አይንፈጉን።
http://windows.microsoft.com/en-US/windows7/Connect-to-a-projector
http://en.wikipedia.org/wiki/Projector

No comments:

Post a Comment