Pages

Sunday, May 6, 2012

ETV ሲዋሽ DireTube ሲያጨበጭብ

  • የተባለው እውነት ከሆነ መንግስት ለምንድነው ግለሰቦቹን ለፍርድ ያላቀረባቸው?????

ይህንንም የምልበት ምክንያት የውጭ ዜጋ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ መግባት ህገዎጥ ስለሆነ ነው። ስለዚህ መንግስት እነዚህን ግለሰቦች ለፍርድ ቢያቀርብ የሀገሪቱም ሕግ ይደግፈዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ለማድረግ እንደማይፈራም በእስር ላይ ያሉትን ሁለቱን የስዊድን ዜጎች ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

  •  የውጭ ዜጎቹ ዜግነት ለምን አልተገለፀም?????


መንግስት የስዊድንን ዜጎች በግልፅ ለፍርድ ካቀረባቸው፣ ለምንድን ነው የአንዲት የመካከለኛ ምስራቅ ሀገር ዜጎችን ዜግነት በግልፅ መናገር ያዳገተው? ነገሩ እውነት ቢሆን ኖሮ የግለሰቦቹን ዜግነት መግለፅ ባላዳገተው ነበር። ነገር ግን ዘገባው የፈጠራ ስለሆነ በአንድ ሀገር ላይ ማላከክ፣ ከተዎንጃዩ ሀገር ትልቅ ጥያቄ ልያነሳና መንግስትን የዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ውስጥ ሊከተው ይችላል።

  •  መንግስት እራሱ ሰዎቹን ላለማምጣቱስ ምን ማስረጃ አለን???

ይህንን ደግሞ ማድረግ ለመንግስት በጣም ቀላል ነው። አህባሾች እራሳቸው የመጡት ከሊባኖስ በመሆናቸው ሁለት የአረብ ወጣቶችን በቀላሉ ከሊባኖስ ሊያስመጡና መንግስት ለፕሮፓጋንዳነት እንዲጠቀምበት መንገዱን ሊያመቻቹ ይችላሉ። በዚያውም ለሁለቱ ወጣቶች ሽር ሽር ይሆናቸዋል። Of course, ትንሽ የገንዘብ ጉርሻም ይሰጣቸዋል።

  • ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ ሁለቱ የውጭ ዜጎች በ24 ሰአት ከሀገር እንዲወጡ መደረጋቸው ነው። ልብ በሉ፣ እንደ መንግስት ዘገባ እነዚህ ሰዎች ከውጭ ሀገር ድረስ ረብሻ ለመቀስቀስ የመጡ ናቸው። ታዲያ እንዴት ተደርጎ ነው በ24 ሰአት ከሀገር እንዲወጡ የሚደረገው? መንግስት እንደመንግስትነቱ እነዚህ ሰዎች ላይ ምርመራ ማድረግ የለበትምን? ለምሳሌ ማን ከህዋላቸው እንዳለ? ምን አይነት network እንዳላቸው? የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊቀርቡላቸውና ሊመረመሩ አይገባቸውምን? ሁላችንም እንደምናውቀው ሁለቱ የስዊድን ዜጎችና አንድ የUN ሰራተኛ በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ ናቸው። ታዲያ የስዊድን ዜጎችንና የUN ሰራተኛን መመርመርና ማሰር ያልፈራ መንግስት ለምንድን ነው እነዚህን የውጭ ዜጎች ማሰርና መመርመር ያልፈለገው??????

ይህ ሁሉ የሚያሳያን ዘገባው የፈጠራ ወሬ መሆኑን፣ የሙስሊሞች ተቃውሞ ላይ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠርና፣ እንዲሁም ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ ጥርጣሬ በመፍጠር ከሙስሊሞች ጎን እንዳይቆሙ እየተደረገ ያለ ፕሮፓጋንዳ ነው። ለማንኛውም እኛም ነቅተንባቸዋል።

1 comment:

  1. Seriously?
    eski contact me info@diretube.com

    ReplyDelete