Pages

Monday, May 14, 2012

The full interview of PM Melese with Tom Walsh


The master mind of EPDRF, Prime Minister Meles Zenawi, had an interview ahead of the world economic forum meeting with Tom Walsh of CCTV. I was wondering what especial question he will raise. I was able to access the translated and trimmed from the daily news of ETV website, then I went to diretube that is where you get in to trap of intelligence agent. Here is to you guys don’t ever never click on ads in diretube, don’t comment which you only spread word of hater, don’t like in facebook, don’t follow them on twitter. If you really love your people and your country just start it today, boycott it.
In the interview Tom had asked, our “beloved and well ruling prime MinisterJ” about upcoming election of 2015.This part you will not find it in ETV news and diretube.  Since I am a fun of free and fair media I always wonder the mathematics of government media. Here is how it works
  1.        If they killed, the number of causality= the number of dead/ 10 for example if seven died that means 0.7. In news they will say it one man had been seriously injured due to suffocation. lool
  2.        If they injured, a number of police officers were injured
  3.        If they give interview for foreign media subtract from it and present part of it to the public.
  4.        When they speak about GDP, multiply it!  
  5.        I don’t know where they use the commutative property of our grade school A+B= B+A

In that media the icon of EPDRF had said he will not participate in any elected government position. So where he will be may be president? This is appointed government position. I suspect we will have a puppet prime minister like Haylemariam Mamo.
 Any way guys here  the  interview! I need your comment which will help me improve my week side!  

Friday, May 11, 2012

የፖለቲካ ጥገኝነት


አንዳንድ ሰዎች በሰው ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቁ ሌሎች በሃገራቸው የፖለቲካ ጥገኛ ሆነው ይኖራሉ. ሁለቱንም ከማይደግፉት ነኝ- እንደዛ አይነት ሰዎች ካሉ ማለቴ ነው
በሰው ሃገር የሚኖሩት ግን ሁለት አይነት ናቸው
1.   የቀድሞ መንግስት ባለስልጣናት
2.   የአሁኑ መንግስት ተቃዋሚዎች
a.   ስልጣን ጥማት ያለባቸው
b.   የህዝብ በደል ያንገሸገሻቸው
በሃገር የሚኖሩት ግን አንድና አንድ አላማ ነው ያላቸው ይከውም ህዝቡን ከሚጨቁኑት ጋር በማበር እሱም የድርሻውን ለመወጣት የሚሞክር፣ የህዝቡን ድምጽ ከሚያፍኑት ጋር አብሮ ማፈን፣ የህዝቡን ሀብት መቀራመት፣ማሸሽና ባለስልጣናቱ ሲያሸሹ የጣሉትን እየተከተሉ ወደ ኪስ ማስገባት.
ማን ነበር ‹እኔ ስገባ እሱ ይወጣል› ብሎ የዘፈነው አይ አመል አለ አመለኛ!

የሚከተሉት ለጊዜው በሀገር ውስጥ የሚኖሩ የፖለቲካ ጥገኞች ናቸው ብዬ አምናለሁ

  1. ግርማ ወ/ጎርጊስ
  2. አቶ አላ ሙሂዲን
  3. ሃይሌ ገ/ስላሴ
  4. ልደቱ አያሌው
  5. ሰለሞን ተካልኝ (አርፊት)
  6. ነዋይ ደበበ 
  7.  የሀይማኖት አባቶች
  8. ጋዜጠኞች(የመንግስት)
From those some need to see doctor. 
In my up coming blog post I will have
  • The three face of Solomon, man, angel and evil
  • Real story of diaspora in meeting 


Sunday, May 6, 2012

ETV ሲዋሽ DireTube ሲያጨበጭብ

  • የተባለው እውነት ከሆነ መንግስት ለምንድነው ግለሰቦቹን ለፍርድ ያላቀረባቸው?????

ይህንንም የምልበት ምክንያት የውጭ ዜጋ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ መግባት ህገዎጥ ስለሆነ ነው። ስለዚህ መንግስት እነዚህን ግለሰቦች ለፍርድ ቢያቀርብ የሀገሪቱም ሕግ ይደግፈዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ለማድረግ እንደማይፈራም በእስር ላይ ያሉትን ሁለቱን የስዊድን ዜጎች ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

  •  የውጭ ዜጎቹ ዜግነት ለምን አልተገለፀም?????


መንግስት የስዊድንን ዜጎች በግልፅ ለፍርድ ካቀረባቸው፣ ለምንድን ነው የአንዲት የመካከለኛ ምስራቅ ሀገር ዜጎችን ዜግነት በግልፅ መናገር ያዳገተው? ነገሩ እውነት ቢሆን ኖሮ የግለሰቦቹን ዜግነት መግለፅ ባላዳገተው ነበር። ነገር ግን ዘገባው የፈጠራ ስለሆነ በአንድ ሀገር ላይ ማላከክ፣ ከተዎንጃዩ ሀገር ትልቅ ጥያቄ ልያነሳና መንግስትን የዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ውስጥ ሊከተው ይችላል።

  •  መንግስት እራሱ ሰዎቹን ላለማምጣቱስ ምን ማስረጃ አለን???

ይህንን ደግሞ ማድረግ ለመንግስት በጣም ቀላል ነው። አህባሾች እራሳቸው የመጡት ከሊባኖስ በመሆናቸው ሁለት የአረብ ወጣቶችን በቀላሉ ከሊባኖስ ሊያስመጡና መንግስት ለፕሮፓጋንዳነት እንዲጠቀምበት መንገዱን ሊያመቻቹ ይችላሉ። በዚያውም ለሁለቱ ወጣቶች ሽር ሽር ይሆናቸዋል። Of course, ትንሽ የገንዘብ ጉርሻም ይሰጣቸዋል።

  • ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ ሁለቱ የውጭ ዜጎች በ24 ሰአት ከሀገር እንዲወጡ መደረጋቸው ነው። ልብ በሉ፣ እንደ መንግስት ዘገባ እነዚህ ሰዎች ከውጭ ሀገር ድረስ ረብሻ ለመቀስቀስ የመጡ ናቸው። ታዲያ እንዴት ተደርጎ ነው በ24 ሰአት ከሀገር እንዲወጡ የሚደረገው? መንግስት እንደመንግስትነቱ እነዚህ ሰዎች ላይ ምርመራ ማድረግ የለበትምን? ለምሳሌ ማን ከህዋላቸው እንዳለ? ምን አይነት network እንዳላቸው? የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊቀርቡላቸውና ሊመረመሩ አይገባቸውምን? ሁላችንም እንደምናውቀው ሁለቱ የስዊድን ዜጎችና አንድ የUN ሰራተኛ በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ ናቸው። ታዲያ የስዊድን ዜጎችንና የUN ሰራተኛን መመርመርና ማሰር ያልፈራ መንግስት ለምንድን ነው እነዚህን የውጭ ዜጎች ማሰርና መመርመር ያልፈለገው??????

ይህ ሁሉ የሚያሳያን ዘገባው የፈጠራ ወሬ መሆኑን፣ የሙስሊሞች ተቃውሞ ላይ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠርና፣ እንዲሁም ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ ጥርጣሬ በመፍጠር ከሙስሊሞች ጎን እንዳይቆሙ እየተደረገ ያለ ፕሮፓጋንዳ ነው። ለማንኛውም እኛም ነቅተንባቸዋል።

Monday, April 30, 2012

Free and fair media.

While seeking for information either to empower yourself or to quote a line what you should care is source. It is obvious that government Medias are the primary source of information, especially for those in third world. But the accuracy is in question most of those countries are under dictators’ control. Printed, audio visual, streamed audio and video and published pages are most of the media we use to our information need or entertainment.

Under are my personal view on some of information source for Ethiopian community

  1.   ETV > the national television service which has hourly news. But I can feel the pain of the news reader once the read all the lies they may say to “Oh! How was it? Am I sweating? Next time I have to wear helmet!”  They even the camera man in front of them.  We have no idea if those cameras in ETV production center have a sniper that shoots if they speak the truth.
  2. ESAT> Washington based satellite television. They are always negative to what is going on in the country. What so ever the government is doing they have never appreciated. I don’t know how they get the budget to sustain them self like infrastructure cost and wedge. Even though the Diaspora is their main target group they are responsible to not mislead and misinform the nation. To avoid the hater among the different group, to motivate Diaspora to participate in the ongoing development of the country. They claim they are independent, are they?
  3.   Allcomtv.com> online streaming service for ETV, TVoromia, Al Jazeera, France 24 and Russia today. I have no intelligent guess on owner but I suspect some connection with ETV itself. For sure we have a clue that the owner is not a foreigner. And if it was not owned by the government they could have a home for ESAT which is the only voice of the oppositions.
Dearest follower on my next post I will give a deep analysis on diretube.com, ethiotube.net, ethiopianreporter.com and leave me your favorite news source as a comment so that I can look at it.

ህዝቡም አዋጅ አወጀ መንግሲቲም ጅሃድ አደረገዉ

ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነፃነትን ፊልጋ ያልፈነቀለው የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን አዋጅን ያውጅ ይሆናል እንጂ ጂሃድን አላወጀም ያውጃልም የሚል ስጋት የለኝም። አወጀ ሲሉ እንኳን በማን ላይ በኬንያ፣በሱዳን፣በሶማሊያ ወይስ በኢትዮጵያ?። አቦ እናንተ እኮ እኔን ታናግሩኝ ጀመራቹ ። ይልቅ የህዝቡን ጥያቄ በቀጥታ መመለስ የተሳነው የመለስ አሰተዳደር የህዝቡን ሰላማዊ ተቃውሞ ለግል ጥቅሙ እያዋለው ይገኛል። ይሀውም ባለፈው አርብ በአሩሲ የተገደሉ ንፁሃን ሙስሊም ወንድሞቻችን አበይት ምሳሌ ናቸው። አቤ ቶክቻው እንዳስነበበን ከሆነ ሼህ ሱዑድ ሻሸመኔ በተካሄደዉ ስብሰባ ላይኢህአዴግን ለሀያ አመታት ስንደግፈዉ ኖረን አሁን እንዴት አሸባሪ አክራሪ ብሎ ይወነጅለናልብለው ነበር። በመሆኑም እኝህ ሰው ትንሽ ከታገስኳቸው ለህዝቡ በስብሰባው የተደረገውን ጨምሮ በድሬ ስለተካሄደው ሚስጥራዊ የአህባሽ አስተምሮ ጠመቃ  ሹክ ሊሉ ይችላሉና ሰበብ ፊጥረን እናስወግዳቸው ይመስላል። “ሊያስሩት የፈለጉትን ሼህ የአልቃኢዳ መሪ ነው! ” ይላሉ አለ አሽብር! 
የባሌ ሙሰሊሞች ግን መቼ ነው እፎይ! የሚሉት ሲወርድ ሲዋረድ መንግስት ቢቀየርም ለነዚህ ህዝቦች ያለውን አመለካከት የቀየረ ይመስላል እንጂ አይቀይርም። እነሱም ጥንካሬ ከሚነላህ ተሰጥቶአቸው አይንገዳገዱም። አቦ አላህ ፈጣሪ ይጨምርላቸው። መሌ አሚን አትልም? ድሮ የዚህ አካባቢ ሰው ቃሊቻ ይሉት ነበር እነሆ ወሃቢያ አሉት ከዛም አልቃኢዳ ጨመሩለት። ምን ነበር አልቃኢዳ? መንግስት ግን አሁን አገሪቱን መግዛት የከበደው ይመስላል። ለአገዛዝ እንዲመች ተከፋፈልን በክልል ግን በቂ አይደለም በመሆኑም በሃይማኖት መከፋፈል አማራቹህ በሃይማኖት መክፈል ግን ቀላል አይደለም እኮ ለነገሩ እርጉዝ የአውራ ዶሮ እንቁላል አማረኝ ብትል ምን ማድረግ ይቻላል?። 

ህዝቡም አዋጅ አወጀ አዋጁም « መንግስት ሆይ! ሀገሬን ምራ እንጂ ቤቴን ለኔ ተውልኝ እኔም ለልጄ እማኖትን አሰተምረው ቢሆን እንጂ አልመርጥለትም!» ግና መንግስት ጅሃድ አደረገው። በፓርላማም ተናገረ። በአሩሲም ገድሎ አስነገረ 7 ግድሎ 10 እንደቆሰሉበት። ይሁና! 

Wednesday, December 14, 2011

ያልተለቀሰለት ሙአች!

ሙሃመድ ቡአዚዚ (27)፡- ታህሳስ 17, 2010 ለቱኒዝያ ለውጥ እራሱን ሰዋ ህዝቡም በልቶ ማደሩን ሳይሆን ለተተኪው የሚያስተላልፈው ነገር ነበርና ሚያሰጨንቀው መልስ ለመስጠት ጊዜ አልወሰደበትም። በእርግጥ ቡአዚዚ በህይወቱ እራሱን ለማጥፋት የሚያነሳሳው ሱሱ ነው ወይስ ሃገር ስትገደል ስትታፈን ለማየት አልፈልግም ማለቱ ነው? ስለ ቡአዚዚ የተፃፉ ማጣቀሻዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን, ሃገር ወዳድ, ድህነትን ለማሸነፍ የሚሰራ, በትምህርቱ ካለበት የምጣኔ ሃብት ችግር የተነሳ ብዙም ያልገፋ ቢሆንም ግን ታናሾቹን እያስተማረ የነበረ ከሱሱ ጋር ምንም አይነት ግኑኙነት የሌለው። ግና መንግስት በህዝቡ ላየሚሰራውን አሻጥር ደባ በደል አይቶ ማለፍ ያልቻለ፣ ስራ አጥነት አድሎና ማግለል በሙስና የተዘፈቀ አሰራር ያማረረው  በመሆኑ ነበር። ይህን ያየ ህዝበ ቱኒዝያ የሰን ማገገም በጉጉት ሲጠባበቅ መንግስትም የተወሰነ የህክምና እርዳታ እያደረገለተ 18 ቀናትን መኖር ቻለ። በሆስፒታል በነበረበት ወቅትም የሚቃወማቸው ፕሬዝዳንት በመምጣት የተሻለ የህክምና እርዳታ ፈረንሳይ ሂዶ እንደ ሚያገኝ ቃል ገቡለት። ግና አልተደረገም ወይም አልተቻለም። ሄደ ላይመለስ, ግና እረፍተ ዜናውን የሰማ ህዝበ አረብ አለቀስ, የቻለም ቃል ገባ "ለሞትህ ምክንያት የሆኑትን እናባርራለን! " በሚል ዜማ። ቀብሩንም የጀግና አቀባበር ተቀበረ ከ5000 በላይ ለቀስተኛ ተሳታፊ ሆነ። ህዝቡም ቃሉን አከበረ ለጎረቤት ሃገር ህዝቦችም ትሚህርት ሰጡ። የዛ ህዝብ ተሞክሮ ለግብፅ፣ አልጄርያ፣ የመን፣ ሶርያ እንዲሁም የተለያዩ ይዘት ያላቸው የመብት ጥያቄዎች በአለም ተንሰራፉ የተወሰኑት ተሳኩ ሌሎች እስካሁን ተስፋ ባለመቁረጥ እየተካሄዱ ይገኛሉ።
ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባው የኛው ሰው እስቲ ህዝቤ ቢያለቅስልኝ በሚል እራሱን በእሳት አያያዘ። የኔሰው ገብሬ (35)። ህዝቡ  ሊያለቅስለት ሲገባ ያለቀሰበት ጀግና። በፖለቲካ አመለካከቱ ከስራ ተባረረ ሞቱም ከእብደት ጋር ተያያዘ ለማዳንም ምንም አይነት ሙከራ አልተደረገም በእርግጥ እብድ ከነበረ ለምን የተሻለ ቢያንስ ሪጅናል ሆሰፒታል አልተወሰደም? ለነገሩ ምን ያረጋል 1 ሰው ለዛውም የኔሰው ቢሞት ነው ሚሻለው ወንድም የለውማ ደሙን የሚፋረድ ፍትህን ሚያነፈንፍ ። ለመሃላው ሳይሆን ለደሞዙ የሚሰራ ዳኛ፣ አቃቢ ህግ እና ጠበቃ። ሃኪሙም ህዝቡን ከመርዳት ይልቅ መጉዳት የሚመኝ በስሙ ከሚነግዱት ጋር አብሮ የሚነግድ። መሃንዲሱም፣ ሙሁሩም ህዝቡም ለእድገት ማነቆ የሆነበትን አሰራር ከማውገዝና ከማስወገድ ይልቅ በአዩኝ አላዩኝ  ብቅ ጥልቅ የሚያጉረመርም። አኗኗርን  ከቀንድ አውጣ የተማረበት አመፁም የቀንድ አውጣ ኑሮውም የቀንድ አውጣ የሆነ ህዝብ ተፈጠረ። ይቀጥላል......